እንኳን ወደ ሂውስተን ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን የአባላት ድረ-ገጽ በደህና መጡ፡፡
ኑ በእምነት እና በአገልግሎት አብረን እንድንድግ ።

አዲስ አባላት

ወደ ቤተክርስቲያናችን ማህበር በደስታ እንቀበላችኋለን። አባል መሆን በአምልኮ፣ በአገልግሎት እና በማህበራዊ ፕሮግራሞች እንዲሳተፉ ያስችላል።

አባልነት ለመመዝገብ

ነባር አባላት

አባል ከሆኑ ፕሮፋይልዎን ለማስተዳደር እና ከቤተክርስቲያኑ ስርዓት ጋር ለመገናኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፡፡

✝️ የአባልነት በረከቶች

በክርስቶስ በማመን በአብ፤ በወልድ፤ በመንፈስ ቅደስ ስም ከተጠመቀ በኃላ ማንኛውም ሰው ክርስቲያን ይሆናል።

ክርስቲያኖች ከጥምቀትም በኃላ የሚከተሉትን በረከቶች ያገኛሉ፤:

  • እግዚአብሔር በሚሰጠው የልጅነት ጸጋ ወራሽ መሆን፤
  • የበዯሌን እና የኃጢያትን ሥርየት ይቀበላል፤
  • በቤቱ ልጅና ወራሽ በመሆን ከእርሱ በሆነ ጸጋ የመንፈሳዊ በረከት ሁለ ተካፋይ ይሆናል፤

በመሆኑም ጥንታዊና ታሪካዊ በሆነች በአንዲት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ጥላ ሥር በመሆን በአጥቢያችን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ህብረት ሲኖረን የምናገኘው የማይቋርጥ ጸጋና በረከት ነው። ስለዚህ የሂውስተን ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕድ ቤተ ክርስቲያን ከላይ ከተገለጸው መንፈሳዊ በረከት በተጨማሪ የሚከተሉትን መንፈሳዊ አገልግሎቶች ይሰጣል፦

የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች:

  • ጥምቀት፤ ተክሊል፤ እና ጸሎተ ፍታት፤
  • መንፈሳዊ የካህናት የምክክር አገልግሎት
  • ህጻናትና ወጣቶች የኃይማኖት ታሪክ ባህልና ቋንቋን፤ ማስተማር፤
  • የአባልነት ማስረጃና የድጋፍ ወረቀት፤
  • የቤተ ክርስቲያን አዳራሽና ሌሎች ክፍሎች በቤተ ክርስቲያኑ መመሪያና ውስጠ ደንብ መሰረት ጉዳይ ሲኖረዎት መጠቀም፤
  • በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ውስጥ መሳተፍ፤ መመረጥና መምረጥ፤
  • ሌሎችም የአባልነት በረከቶች አሉት፤

መዋጮ

የእርስዎ ልግስና ቤተክርስቲያናችንን እና መርሃግብሮቻችንን ለመደገፍ ይረዳል::

የአባልነት መዋጮ/ልገሳ ይስጡ

እገዛ ይፈልጋሉ?

📧 membership@houstonmedhanealem.org
📞 (346) 333-0755